fredag 22 september 2017

http://welkait.com/?p=9989

የአማራ ህዝብ የወደፊት ውስጣዊ ፈተና ርዕዮት አለም ሳይሆን ስሜት ነው።

Print Friendly, PDF & Email
(አያሌው መንበር )
ላለፉት ጥቂት አመታት የመጣንበት ጊዜ ሲቃኝ አማራው ላይ እየደረሰ ያለ ግፍን የማሳወቅ እንቅስቃሴ ነበር። በማሳወቁ በኩል እንደ እነሞረሽ ያሉ እና በግላቸው እንደ እነ ዶ/ር አሰፋ ያሉ ምሁራን ከመዓህድ ቀጥለው ታሪክ የማይረሳቸው ናቸው። ይህንን የማሳወቅ ስራ ለህዝብ ተደራሽና በሚፈለገው መንገድ ህዝቡን ለአፀፋ በማዘጋጀት በኩል ግን እነዚህ አካላትን በእጥፍ ያስከነዳው የአማራ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ አዲሱ የአማራ ትውልድ ነው።እናም የማሳወቁ ሰነድና መረጃ የማዘጋጀት ጉዳይ እና ከወጣቱ ጋር ተቀናጅቶ ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ አይደፈሬ የአማራነት ግድግዳ ተሰርቷል።
ከዚያ ማግስት የነበረው ሂደት መደራጀት ነው። ይህ የሂደት ውጤት የሆነ ተግባር ትልቅ ጉልበት የሚጠይቅ ነው። በዚህ ውስጥ አሁንም ያልተሻገርናቸው የሚመስሉ ጥቃቅን ተግባራት ቢኖሩም ቢያንስ አሁን በትልቁ አማራው መደራጀት አለበት የሚለው ተረጋግጦ አደረጃጀቱ ተመስርቷል። ከዚህ አደረጃጀት ላይ ሁለት ፈተና ተጋርጧል።
አንደኛው አደረጃጀታችን ሀገራዊ ስዕል ይያዝ የሚለው ፍሬው የረገፈ ሾላ ሲሆን ሌላኛው አማራዊ ይዘት ብቻ ይከተል የሚለው ነው። ይህ ሁለተኛው አዋጩና አሸናፊው ሀይል ለመሆኑ ማረጋገጫው የአማራውን ጉዳይ ተደራሽ ባደረገው በወጣቱ ዘንድ ያለቅድመ ሁኔታ ተመራጭ መሆኑና ነባራዊ ሁኔታውም ይህ መሆኑ ነው። ይህ ስልት ፈተናው ብርቱ ውጤቱ ግን ወደር የለሽ ነውና ቀጣይነቱ አያጠራጥርም። የሚፈጠሩ እና እንቅፋት የሚበዛባቸው አጀንዳዎች እስካሁን አሸናፊ መሆናቸው ይህንን አስተሳሰብ የበለጠ ስኬታማ እንደሚሆን ተጨማሪ ማረጋገጫም ነው።
ሆኖም ይህ መነሻውና መዳረሻው አማራ ላይ የሆነና ምናልባትም እንደሀገር ለመቀጠል ትልቅ እርሾ የሚሆነው የምርጫ ሳይሆን የውዴታ ግዴታ አማራነት ጉዳይ አሁን ላይ ዋናው ምዕራፍ ላይ ትልቅ ፈተና ተጋርጦበታል። ይህ ወቅት ብዙ ሰዎችን ዳምጦ አልያም ውጦና ረግጦ ካልወጣ በስተቀር ወጀብ ይመታውና የቀን ጅብ ይበላዋል። ይህንን አማራነትና በደል ያሰባሳበው የተነቃቃ ሀብት ከጉሯሯችን ሊነጥቀን ያሰፈሰፈ ሀይል አለ። በአንድ በኩል በከሸፈው የአንድነት ጓዳ ውስጥ ለማስገባት እጀ ረጅም ሰዎች መረባቸውን ዘግርተዋል። በሌላ በኩል ወትሮውንም “እምየ” የሚል ቃል ብቻ ሲሰማ እምባ የሚተናነቀውና ወገኑ ስለሆን ብቻ በቅርበት ያለው ሀይልም ወደዚያ እንድንጓዝ እየገፋን ነው። ሁለቱም ግን ለእኛ ተመልሶ የስቃይ አረንቋ ውስጥ መዘፈቅ ነው።
ይህ ስጋ እንዳየ ጥንብአንሳ ያንዣበበው እና በራሱ መንገድ ተጉዞ ስንቴ የከሸፈው የእሳት ራት ትውልድ አካሄድ በተካነበት የሴራ (Conspiracy) አካሄድ ታግዞ ከዋናው ጠላታችን ባልተናነሰ መንገድ በተለይም በቅርብ ወራቶች ውስጥ ክንፉን ዘርግቷል።ይህ አደገኛ ነው።አካሄዱም የተጠና ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አኛ ራሳችን ላይ የሚታይ የፖለቲካ አቅም ማነስ የወቅቱ ፈተናችን ነው። ይህ ማንም ሊክደው የማይችል የአደባባይ ሚስጥር ነው። ምክንያቱ ደግሞ ብዙዎቻችን ተግባርና ነባራዊ ሁኔታ የመራን የደራሽ ጎርፍ ያመጣን እንጅ ህይወታችን ፓለቲካ ይሆናል ብለን አቅደን የገባን አለመሆናችን ነው።#ከእውቀታችን ይልቅ #ስሜታችን እየቀደመ፣ ከስልት ይልቅ ጉልበት እያሸነፈ፣ ከአብሮነት ይልቅ ግለኝነት እየገዘፈ፣ በአማራነት ውስጥ አካባቢያዊነትና እምነት እንደወጀብ እየመቱን ወሳኝ የሽግግር ወቅት ላይ እንገኛለን። ይህ እጅግ የምንፈተንበት ወቅት ነው።
#በመፍትሄነትም
#ለብሄሩ ታማኝነትን እንደመርህ ሁላችንም ልንታጠውቀ ይገባል። ቀበቷችን፣ ዝናራናችን፣ መቀነታችንም #አማራነት ብቻ መሆኑን ልናሰምርበት ይገባል።
#ስሜትን መቆጣጠርና የግል ፍላጎታችን ቢነካ እንኳን ብዙሀኑን ማስቀደምን መርህ ማድረግ። ያማረ ሁሉ አይበላም በለውል መርህ ለፅሁፎቻችን፣ ለንግግግራቻችን፣ ለአሽሙሮቻችን ወዘተ ሁሉ ልንጠነቀቅ ይገባል። የግል ስሜት የህዝብ ስሜትን ገደል የአከት ነው።
#ለወደፊቱ መሪ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ራሳቸውን አዘጋጅተው የሚገኙበት የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው የመሪነትና የፖለቲካል ሳይንስ እንዲሁም አለማቀፍ ግንኙነት ጉዳዮች ስልጠና ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል። እዚህ ላይ የድርጅታዊ አቅም ግንባታ ስልጠና በቀዳሚነት ሊያዝ ይገባል።ከስብሰባ ይልቅ ስልጠና ላይ ልናተኩር ይገባል። አሁን መስመራችን በደንብ ልንፈትሽና ልናጠራ ይገባል። ይህ ወቅት ግድግዳችን እንዲጠነክር ማገር የምንማግርበት ወሳኝ ወቅት ነው።
#ከዚህ በፊት የከሸፈው አንድነት ይከተለው የነበረውን የዝንጀሮ መንጋ ዘመቻና ከአማራ ስነምግባር ያፈነገጠ አገላለፅንና አተጋገልን መናቅ ይጠይቃል። እዚህ ላይ እርሱማ እንዲህ ነው እርሷማ እንዲህ ናት እያለ የአንድነቱ ሀይል ያደርገው የነበረው የቡና ቤትና የፓልቶክ ትግልን እንደአማራን ልንፀየፈው ይገባል።እዚህ ላይ ቀድመው ፊት ላይ የነበሩ እና አሁንምፊት ላይ ያሉ ልጆች የትግል ስልታችን እንደገና አልፎ አልፎ #ለማስታወስ የቀድሞ ፅሁፎችን ማምጣ እና የመከለስ ሀላፊነት ሊወስዱ ይገባል።
#ሌላው ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ከእኛ የተሻለ ሰው ይመጣል ብሎ ማመን ነው። አማራው የምሁር ባለቤት ነው። ግን በተለያየ መንገድ ፊትለፉት አልተሰለፈም። ይሁንና አልፎ አልፎ ብቅ ብቅ ሲል በሚሰነዝረው ሀሳብ ሳይህላን ገና ቀድሞ አልነበረም በሚል እዳይሳተፍን በሩን እየዘጋንበት ነው ብየ እገምታለው። ስለዚህ ሁልጊዜ መናፈቅ ያለብን ከእኛ የተሻለ ሰው እንዲመጣና እንዲያግዘን እዳይመንጣ በሩን በመዝጋት መሆን የለበትም። ((ይህንን በምፅፍበት ሰዓት አሁን እንኳን አንድ ወዳጀ አስገራሚ ትንታኔ ልኮልኝ እየተደመምኩ ነው ያነበብኩት። ሰዎች አድፍጠው ያዩናል። ለመቅረብ ይፈሩናል።ግን እኛም እንዳይቀርቡ እየገፋናቸው ነውና እንጠንቀቅ።))
ይህ ሲሆን ባለማወቅም ይሁን በመሰልቸት እየገፋን ሊጥለን የሚደርሰውን ስሜታችን አሸንፈን የአላማችን ግብ ለመድረስ እቅፋቱ ቀላል ይሆናል።

Inga kommentarer: